የኢትዮጵያውያን  መረዳጃ ዕድር በሲድኒ
Ethiopian Friendship & Co-Operative IDIR In Sydney
                                    Est. 2010                                    we can not direct the wind but, we can adjust the sails.
ከሀገራችን ባህልና ወግ ብዙም ባልራቀ ዘይቤ ተመክሮበት የተቋቋመ ዕድር ነው          ለዕርስዎ ከቤተሰብዎ ለቤተሰብዎም ከእርስዎ በላይ የለምና ዛሬን በነገ መነጽር አጥንተው ድንገት ከሚከሰት ችግር አድነው ዕርስዎም ይዳኑ!          አመቺ መንገድ በመሰልዎት ቢያገኙን ጠቀም ያለ ማብራሪያ ያገኛሉ! ለአስተዋይነትዎም ልናመሰግንዎት እንወዳለን!!
coming soon memb.form
Ethiopian Cooperative IDIR in Sydney
We would like to read your valuable comment, suggestion and question
 to support our fast progress.
 First Name   
   Last Name 
        E-mail    

 Comments: (Max 500char)


«ሁሉ ሰው ለነገ ያስባል። የመጨረሻው ግድ የለሽ ባይ ነገን እያሰበ ይጨነቃል። እንቅልፍ ይነሳዋል። ዛሬ ማንም ሰው ሲተኛ ነገ እንደሚነቃ ጠብቆ ነው። እራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች እንኳን ነገነ አስበው ነው፤ ነገ እንደማይቀናቸው አስበው ነው፤ የነገው መልከ ቀና ቀጠሮ እንደማይሰምር ተሰምቷቸው ነው። ለነፍሴ አደርኩ የሚሉ ቅዱስ እንኳን ነገ፤ ከነገ ወዲያ መምጫው የማይታወቅ ዓምላክ በመንግስቱ እንዳይረሳቸው ይመኛሉ። ዛሬን ደግ ይሰራሉ፤ ዛሬን ይራባሉ፤ ዛሬን ይጠማሉ፤ ዛሬን ይቀድሳሉ፤ ዛሬ ዛሬ ደግ ይናገራሉ፣ ይዘምራሉ፣ ይጸልያሉ፣ ይመጸውታሉ። ነገ የሚዘነጋ አይደለም። ነገ ለዓለም ህዝብ ህመም ነው። ከፕሬዝዳንት እስከ ለፕሬዝዳንት እስከሚያጨበጭበው። ከሰው እስከ እንስሳት የነገ ነገር የማያብሰለስለው የለም። ቢለያይ «የነገዎች» እርዝመት ነው። ቢለያዩ ሊሰየም በሚከብድ ደረጃቸው ነው እንጂ የነገ ነገር የማያስደነግጠው የነገ መምጣት የማያባባው የለም።»
«ግራጫ ቃጭሎች» - ከአዳም ረታ

news..
የሲድኒ የመረዳጃ እድር
የመጀመሪያውን ጠቅላላ ስብሰባ አካሄደ
   (also in pdf)

ኖቬምበር 7 እሑድ በሊድከም አዳራሽ የእድር ምስረታን አስመልክቶ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎችና የተመዘገቡ የእድሩ አባላት በተገኙበት ስብሰባ ተካሂዷል። እድሩን በማሰባሰብና እስከአሁንም ስራውን ሲያካሂድ የቆየው የግዚያዊ ኮሚቴ ም/ዳኛ የሆኑት አቶ እስማኤል ሱሊማን ሕዝቡን አመስግነው ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር “የምንኖረው በሰው ሀገር ሲሆን አብዛኛው ሕብረተሰባችን ግን የዕለት ተዕለት ኑሮውን ለማቃናት ደፋ ቀና ከማለት አልፎ የመኖርን ያህል መሞትም እንዳለ የተገነዘበው አይመስልም” ብለዋል። በዚህ አይነት ሁኔታ መቀጠልም ማብቃት ያለብት ጉዳይ እንደሆነም አስገንዝበዋል። ስለሆነም ብቸኛው አማራጭ የተመሰረተውን እድር በመደጋገፍ ማራመድና ማሳደግ የሁላችንም የትውልድ ኃላፊነት ነው ብለዋል።

በመጋቢት ወር 2010 አጋማሽ ላይ ከተለያየ አካባቢና የኅብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ 14 የስድኒ ነዋሪዎች ስብሰባ አድርገው እድር ለመመስረት ሁኔታዎችን አመቻቹ። ቀዳሚ ተግባር አድርገው የተነሱት አላማውንና ለአባላት የሚሰጠውን አገልግሎት በዝርዝር የያዘ መተዳደሪያ ደንብ ማርቀቅ ነበር። የእድሩ ፀሃፊ አቶ ስሎሞን ከበደ ዓላማዎቹን እንደሚከተለው ገልጸዋል፤
1. በአባል ላይ ሐዘን ሲደርስ የችግሩ ተካፋይ በመሆን መተጋገዝ። ይህም የተመደበውን የገንዘብ መጠን መሰጠት እና ከቀብር ስርዓቱ ጋር ተጓዳኝ የሆኑ ስራዎችን በመስራት አገልግሎት መስጠት።
2. አንድ አባል ወይም የቤተሰቡ አባል ቢታመም ቤተሰቡ በሚፈቅደው መንገድ በመጠያየቅ መተጋገዝ።
3. የተለያዩ ዝግጅቶችን በማድረግ አባላትና ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዲቀራረቡና እንዲጠያየቁ አጋጣሚዎችን መፍጠር። የሚሉት ሲሆኑ መርዶን በተመለከተ ግን እድሩ ምንም ዓይነት የገንዘብ ወይም ሌላ አገልግሎት እንደማይሰጥ ጠቁመዋል።

ፀሃፊው በመቀጠልም አባላት ከእድሩ የሚያገኙት ጠቀሜታ፣ የአባላት መብትና ግዴታ በመተዳደሪያ ደንቡ ውስጥ የሰፈሩትን አንቀጾች በማንበብ አብራርተዋል። የፋይናንስ ሪፖርትና የተዘረጋውን ግልጽ የአሰራር ዘዴ በተመለከተ ገንዘብ ያዥና የፋይናንስ ኃላፊዎቹ አቶ ለማ ብሩና አቶ ግርማ ፈይሳ በቅደም ተከተል ገለጻ አድርገዋል። በመተዳደሪያ ደንቡ እንደሰፈረውም የፋይናንስ ሪፖርት ማለትም ወጪና ገቢ እንዲሁም በየወቅቱ ያለው የእድሩ ካፒታል በጥሬ ገንዘብና ንብረት ለአባላቱ በደብዳቤ/በኢሜል የገለጻል። ከዚያም ከአባላት በቀረቡ ሃሳቦችና ጥያቄዎች ላይ ውይይት ተካሂዷል። በዕለቱም ወ/ሮ ውብዓለም ያሊ ከእድሩ የምስረታ ስብሰባ ጋር ተስማሚ የሆነ ግጥም በማቅረብ ተስብሳቢውን አዝናንተዋል።

በታደለው ፕሮግራም መሰረት ሌላው የመነጋገሪያ አጅንዳ የነበረው የኮሚቴ አባላትን ምርጫ ማካሄድ ነበር። አሁን ያለው ኮሚቴ ግዚያዊ በመሆኑ እድሩ ደግሞ በግዚያዊ ኮሚቴ መቀጠል ስለማያስፈልገው ቋሚ ኮሚቴና የመካሪ ጉባኤ አባላት እንዲመረጡ የስብሰባው መሪ አጀንዳውን ከፍተዋል። ብዙ ሰዎ እጃቸውን በማንሳት ያለው ኮሚቴ ለተጨማሪ አንድ ዓመት እንዲያገልግልና የጀመሯቸውን ስራዎች ማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል ተብሏል። በሌላ በኩልም የኮሚቴ አባላቱ ስብጥር ኅብረተስቡን በሰፊው የሚወክል ሆኖ ስለሚታይ በዚሁ ይቀጥሉ የሚሉና ተመሳሳይ ድጋፎች ተሰንዝረዋል። ያሉት 8 የኮሚቴ አባላት እንዳሉ ሆነው በነሱ ላይ ሁለት አባላት እንዲጨመሩ በተወሰነው መሰረት ወ/ሮ ዓይናለም ተስፋዪና አቶ ሲሳይ ካሴ በአንድ ድምጽ ተመርጠዋል።

ስብሰባው ከመጠናቀቁ በፊትም የእድሩ ዳኛ አቶ ፍቅሩ አበራ የማጠቃለያ ንግግር እንድያደርጉ አቶ እስማአኤል ጋብዘዋል። በአካላቸው ላይ በደረሰው ጉዳት ለጊዜው በማገገም ላይ እንድሚገኙ ገልጸዋል። የእድርን አስፈላጊነት በተለይም ለረጅም ግዜ ሲታሰብ የቆየው የእድር ምስረታ ሃሳብ በተግባር ከግብ ሊደርስ የመቻሉን አድማስ ማየት ለሁላችንም ከፍተኛ ደስታን የሚሰጥ ነው ብለዋል። ዛሬ የተሰጠንን የህዝብ አስተያየት ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ኃላፊነታችንን ለመወጣት የቻልነውን እንሰራለን በማለት ገልጸዋል። ሁላችንም ከተባበርን እድሩን ለከፍተኛ ቦታ ማድረስ ሊከብደን አይችልም በማለት የህዝቡን ተሳትፎ አድንቀው ዝግጅቱ በዚሁ ተጠናቋል።


contact us:
                P. O. Box 279
                Auburn   NSW  1835
                Tel. 0434 287 709; 0404 458 158
                ethiopianidir@gmail.com

bank details:
                Commonwealth Bank (Blacktown)
                BSB No. 062339
                Acc. No. 10548769
   Fonts can be download here if the page is unreadable

Ethiopian Cooperative IDIR in Sydney;     IBN: 'on process';     Registered Licence No.: 'on process';     November 2010